エピソード

  • DW Amharic የነሐሴ 09 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/15
    በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በ71 ልጃገረዶች፣ 29 ሴቶች እና 2 ወንዶች ልጆች ላይ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት መፈጸማቸውን የተባበሩት መንግሥታት እንዳረጋገጠ የዋና ጸሀፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሪፖርት አሳየ። በሁለት ወራት 15,000 ገደማ ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ተመለሱ። ከሶማሊያ መገንጠሏን ላወጀችው ሶማሌላንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እውቅና እንዲሰጡ አሜሪካዊ ሴናተር ጥያቄ አቀረቡ። በፓኪስታን እና በሕንድ የጣለ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ 260 ገደማ ሰዎች ገደለ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በአላስካ ይገናኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/08/14
    የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አርዕስተ ዜና ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች ትናንት የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከሰጠሙ በኋላ የደረሱበት ያልታወቀ ቢያንስ አስር ስደተኞች ፍለጋ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። የእስራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻረን ሀስክል የደቡብ ሱዳንን ጉብኝት ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ ወደ ሌሎች ስፍራዎች የማስፈር እቅድን የተመለከተ አይደለም ሲሉ ሁለቱም ወገኖች ተናግረዋል። የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት የሚያስቆም ስምምነት ላይ የሚደረሰው፣ ነገ አርብ ከፑቲን ጋር በአላስካ በሚያካሂዱት ጉባኤ ሳይሆን በቀጣዩ ሁለተኛው ጉባኤ ላይ መሆኑን አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/13
    -ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሰፈሩ ሰዎች ለተቃጠለ ቤትና ለማያርሱት መሬት ግብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸዉን አስታወቁ።---የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል-ቡርሐን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የአፍሪቃ ጉዳይ ልዩ አማካሪ ማሳድ ቦዉሎስ ጋር ሥለሱዳን ሰላም በድብቅ ተነጋገሩ።-የአዉሮጳ፣ የዩክሬንና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ዛሬ በቪዲዮ ያደረጉት ጉባኤ አግባቢ እንደነበር የአዉሮጳ መሪዎች አስታወቁ።ጉባኤዉ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የፊታችን አርብ በሚያደርጉት ጉባኤ የአዉሮጳና የዩክሬን ፍላጎት እንዳይዘነጋ ለማሳሰብ ያለመ ነበር
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    2025/08/12
    DW Amharic-በዛሬው የዓለም ዜና ፤በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባቦሩ ወረዳ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በታጣቂዎች መገደላቸውን።የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ውጤት ማምጣቱን ኢሰመኮ መግለፁን፣የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች በሰሜን ዳርፉር በተፈቃዮች መጠለያ ጣቢያ ባደረሱት ጥቃት 40 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ብሪታንያ እና ጃፓን በጋዛ «እየተከሰተ» ነው ባሉት ረሀብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቡን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋዛ በአልጀዚራ ጋዜጠኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዙን።ያስቃኛል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 5 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/11
    የኢትዮጵያ አየርመንገድ ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ ለሚገነባው ግዙፍ የአቡሴራ አየርማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች ውክልና ሰነድ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ዛሬ ተፈራረመ፡፡ የናይጄሪያ ጦር ከ100 በላይ «ዓመጸኛ ወንጀለኞች» ያላቸውን መግደሉን አስታወቀ። እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 5 የአልጀዚራና 1 የፍልስጤም የግል መገናኛ ብዙኀን ዘጋቢ መገደላቸውን የጋዛ የስቪል መከላከያ ተቋም እና አልጀዚራ አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • DW Amharic የነሐሴ 04 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/10
    በሰሜን ኮርዶፋን 18 ሰዎች በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጥቃት፤ በኤል ፋሽር 63 ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጦት ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ። ኤርትራውያን ከፈረንሳይ ወደ ብሪታኒያ የቀዘቀዙ አትክልቶች ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ ተገኙ። በናይጄሪያ ወሮበሎች 13 ጸጥታ አስከባሪዎች ገደሉ። እስራኤል ጋዛን ብትቆጣጠር "ሌላ ጥፋት" እንደሚከተል የተመ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሀገራቸው ጋዛን የምትቆጣጠረው ለአጭር ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል። የዩክሬን እና የሩሲያን ጦርነት ለማብቃት የሚፈጸም ሥምምነት ኪየቭን ሊያካትት እንደሚገባ የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ አሳሰቡ።
    続きを読む 一部表示
    8 分
  • የነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/08/09
    በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ባጋጠመ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ። 67 ሰዎችን ከሃገር በሕገወጥ መንገድ ሊያስወጣ ሞክሯል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ፡፡ በደቡብ ጃፓን የምትገኘዋ የናጋሳኪ ከተማ በዩናይትድ ስቴትስ በአቶሚክ ቦምብ የተደበደበችበት 80ኛ አመት ዛሬ ዘክራ ውላለች።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 2 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/08
    -የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደርስበትን እልቂት ለመግታት በሥልጣን ላይ ያለዉን መንግስት በሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሕዝባዊ ትግል መቀየር እንዳለበት የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ጥሪ አደረገ።--የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት መጀመሩን በይፋ አረጋገጠ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሕጋዊ ፓርቲነት ያገደዉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶብረፅዮን ገብረ መድሕን የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥትን ወቅሰዋል።--እስራኤል ያወደመቻትን የጋዛ ሰርጥ ርዕሠ-ከተማ ጋዛ ከተማን በጦር ሐይል ለመቆጣጠር መወሰኗ ከዉጪም ከዉስጥም ዉገዝትና ተቃዉሞ ገጥሞታል።
    続きを読む 一部表示
    12 分