『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

このコンテンツについて

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW 政治・政府
エピソード
  • የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/08/14
    የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አርዕስተ ዜና ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች ትናንት የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከሰጠሙ በኋላ የደረሱበት ያልታወቀ ቢያንስ አስር ስደተኞች ፍለጋ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። የእስራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻረን ሀስክል የደቡብ ሱዳንን ጉብኝት ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ ወደ ሌሎች ስፍራዎች የማስፈር እቅድን የተመለከተ አይደለም ሲሉ ሁለቱም ወገኖች ተናግረዋል። የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት የሚያስቆም ስምምነት ላይ የሚደረሰው፣ ነገ አርብ ከፑቲን ጋር በአላስካ በሚያካሂዱት ጉባኤ ሳይሆን በቀጣዩ ሁለተኛው ጉባኤ ላይ መሆኑን አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/08/13
    -ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ የወለጋ ዞኖች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሰፈሩ ሰዎች ለተቃጠለ ቤትና ለማያርሱት መሬት ግብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸዉን አስታወቁ።---የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል-ቡርሐን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የአፍሪቃ ጉዳይ ልዩ አማካሪ ማሳድ ቦዉሎስ ጋር ሥለሱዳን ሰላም በድብቅ ተነጋገሩ።-የአዉሮጳ፣ የዩክሬንና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ዛሬ በቪዲዮ ያደረጉት ጉባኤ አግባቢ እንደነበር የአዉሮጳ መሪዎች አስታወቁ።ጉባኤዉ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የፊታችን አርብ በሚያደርጉት ጉባኤ የአዉሮጳና የዩክሬን ፍላጎት እንዳይዘነጋ ለማሳሰብ ያለመ ነበር
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    2025/08/12
    DW Amharic-በዛሬው የዓለም ዜና ፤በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባቦሩ ወረዳ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በታጣቂዎች መገደላቸውን።የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ውጤት ማምጣቱን ኢሰመኮ መግለፁን፣የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች በሰሜን ዳርፉር በተፈቃዮች መጠለያ ጣቢያ ባደረሱት ጥቃት 40 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ብሪታንያ እና ጃፓን በጋዛ «እየተከሰተ» ነው ባሉት ረሀብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቡን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋዛ በአልጀዚራ ጋዜጠኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዙን።ያስቃኛል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
まだレビューはありません