エピソード

  • "ልጄ ገዛኸኝ በመኪና አደጋ ከማለፉ በፊት 'እናቴ ይቅር በይኝ' ብሎኝ ነበር፤ ለካስ ስንብት ነው፤ በሕልፈቱ ልቤ ተሰብሯል" እናት ድንቅነሽ አሸብር
    2025/05/23
    "ጌታሁን በጣም ጥሩ ሰው ነው፤ ተፈጥሮን የሚያደንቅ ነበር። ብንለያይም በሕልፈቱ በጣም አዝኛለሁ" በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያለፈ የጌታሁን ዝግታ የቀድሞ ባለቤት ዳናዊት ሕሉፍ። የወጣት ገዛኸኝ ታደሰ ፀሎተ ፍትሐት ቅዳሜ ግንቦት 16 / ሜይ 24 በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን 9:30 am ከተከናወነ በኋል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የሚፈፀም ሲሆን፤ የአቶ ጌታሁን ዝግታ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅርቡ ይከናወናል።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • ኢትዮጵያ ከቻይና - ቻይና ከኢትዮጵያ የሚሹት ምንድን ነው?
    2025/05/22
    በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ የኢትዮ - ቻይና ዲፕሎማሲያዊና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነቶችንና የወደፊት ውጥኖቻቸውን አጋርተው ነበር (የSBS 50ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ዳግም የቀረበ)።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • ከማገብት እስከ ሕወሓት - አምባሳደር ስዩም መስፍን
    2025/05/22
    በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ ከትጥቅ ትግል ጅማሯቸው ተነስተው፤ ከሕወሓት አመራር በፈቃዳቸው ስለምን እንደተሰናበቱ አስረድተው ነበር (የSBS 50ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ዳግም የቀረበ)።
    続きを読む 一部表示
    16 分
  • ለኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገራት የግል ተጓዦች የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ ወደ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ሲል ለንግድ ሥራ መንገደኞች 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተፈቅዷል
    2025/05/20
    የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም አወዛጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማናቸውም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳብ እንዳይሰጡ የሚከለክል ደንብ ፀደቀ
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • "ከአክሊሉ ኃብተወልድ ወዲህ ከተማ ይፍሩ፣ ምናሴ ኃይሌና ይልማ ደሬሳ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ታላላቅ ዲፕሎማቶች ናቸው" አምባሳደር ዘውዴ ረታ
    2025/05/20
    በ77 ዓመታቸው ከአንድ አሠርት ዓመት በፊት ከእዚህ ዓለም ከመለየታቸው በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ዲፕሎማት ከነበሩት አምባሳደር ዘውዴ ረታ ጋር በሙያ ሕይወታቸው፣ የሥነ ፅሁፍ በረከቶቻቸውና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ዙሪያ አተያያቸውን አጋርተውናል። የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግም ዳግም አቅርበነዋል።
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • የአውስትራሊያ ተቃዋሚ ቡድን ሊብራል-ናሽናልስ ፓርቲዎች ጥምረት ፈረሰ
    2025/05/20
    የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ቀነሰ
    続きを読む 一部表示
    5 分
  • "ኢሬቻ ቱሉ / አፍራሳ ኦሮሞዎች እግዚአብሔር ላደረገላቸው ምስጋና፤ ለወደፊቱ ልመና የሚቀርቡበት ነው" ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ
    2025/05/20
    በሜልበርን የኢሬቻ ቱሉ / አፍራሳ ክብረ በዓል አስተባባሪዎች ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ፣ ኦቦ በንቲ ሆሉቃና አደይቱ ሚደቅሳ የክብረ በዓሉን ፋይዳዎችና የአከባበር ሂደቱን አንስተው ያስረዳሉ።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • ለባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደምክንያት ሲጠቀሱ የነበሩት አስገዳጅ የቦንድ ግዢና የብድር ጣሪያ ገደብ የሚደነግጉ መመሪያዎች ሊሻሩ ነው
    2025/05/19
    ሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል ያሉትን የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የጤና ባለሙያዎች ያነሷቸው የደመወዝ፣ የጥቅማ ጥቅምና ምቹ የሥራ ሁኔታ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ካላገኙ ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሳሰቡ፤ የጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ።
    続きを読む 一部表示
    12 分