-
サマリー
あらすじ・解説
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ሲጸድቅ አንድ ባንክ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ቅርንጫፍ ከፍቶ ለመሥራት የሚያስችለውን ፈቃድ ለማግኘት 66 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ሐብት ሊኖረው ይገባል። ረቂቅ መመሪያ ውህደትን የሚገፋፋ እንደሆነ በባለሙያዎች ዘንድ ግንዛቤ አለ። ይህ ውይይት የባንኮች ውህደትን ፋይዳ እና ተግዳሮት ይፈትሻል። በውይይቱ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት አቶ ባህሩ ያሲን፣ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ የባንክ ባለሙያነት ያገለገሉት የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ለማ እና የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ ተሳትፈዋል።