エピソード

  • ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን?
    2025/04/14
    የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003።ዋሽግተን።ሲሞን ሔርሽና ኮኒ ብሩክ የተባሉት መርማሪ ጋዜጠኞች እንደፀፋት የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ መሪዎች የቴሕራኖችን ሚስጥር እንዲያጋልጡ የገፋፏችዉ መረጃዉንም የሰጧቸዉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ናቸዉ።
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታ
    2025/04/07
    የቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»
    続きを読む 一部表示
    14 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ
    2025/03/31
    የብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • ማሕደረ ዜና፣ ሱዳኖች አንድም ሁለትም ሆነዉ ከግጭት-ጦርነት ያልተዩ ሐገራት
    2025/03/24
    የማቻር ደጋፊ የሚባሉት የኑዌር ጉሳ ሚሊሻዎች ኢትዮጵያን በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢ ከሠፈረዉ ከፕሬዝደንት ሳልቫኪር መንግስት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩ ሳምንት አልፈዋል።የጁባዎች ጠብ የናረዉ ጁባዎች ከጋራንግ ሞት በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ ከአል በሽር መወገድ በኋላ ዋና እና ምክትል ሆነዉ የካርቱም ሪፐብሊካን ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት የሱዳን ጄኔራሎች የገጠሙት ጠብ በጦር ሜዳዉም በፖለቲካዉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት መሆኑ ነዉ።የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከደቡብ ሱዳን ቡድናት ካንደኛዉ ጋር ያለዉን ትብብር ከማጠናከርም አልፎ የትይይዩ መንግስት--- ዳርፉር ግዛት ሊመሰርት ይችላል የሚለዉ ግምትም እያየለ ነዉ
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • “መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር
    2025/03/17
    የህወሓት አመራሮች ልዩነት ሲበረታ በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ያለፈው የትግራይ ክልል ነዋሪ “ነገስ ምን ይፈጠራል?” በሚል “እየተሳቀቀ እንዲኖር” ተገዷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ሥጋት “ሰዉ በጣም ተረባብሿል”፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ “መከፋፈል” ተፈጥሯል። ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው “የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ” ነው።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየተንሸራተተች ይሆን?
    2025/03/10
    ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ናስር ከተማ በደቡብ ሱዳን ጦር ሠፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጁባን ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ከቷታል። በናስር በሚገኝ የደቡብ ሱዳን የጦር ሠፈር ላይ ባለፈው ሣምንት ጥቃት የፈጸመው ዋይት አርሚ ተብሎ የሚጠራ የኑዌር ጎሳ ታጣቂ ቡድን ነው። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸው ሪየክ ማቻርን ሳያማክሩ የወሰዷቸው ርምጃዎችም ቅሬታ ፈጥረዋል። ሁለቱ የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ፈርሶ ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ ሥጋት አለ።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ሶማሊያ ወዳጅነት ካንጀት ወይስ ካንገት?
    2025/03/03
    የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች የጠባቸዉን መሰረታዊ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ማስወገዳቸዉን በይፋ ሳይናገሩ በወር ዕድሜ ለመወዳደስ፣ መተቃቀፍ መነፋፈቅ መድረሳቸዉ በርግጥ ጉድ አጃኢብ ማሰኘቱ አልቀረም።ማስታወቂያ ሚንስትር ዳዉድ አዌስ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምነት ተሰርዟል።አዲሱ የትብብር ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ወደብ ሥለ ማስገኘት አለማስገኘቱ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የምክር ቤት አባልናየፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር አብዲ ቡባል እንደሚሉት ደግሞ መተማመንን ለመገንባት ከአዲስ አበባ-ሞቃዲሾ-አንካራ የሚባክኑት ባለሥልጣናት ወደብን በተመለከተ አሁንም አይተማመኑም
    続きを読む 一部表示
    14 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ትዩዩ መንግስት፣ ጦርነቱና የዉጪ ጣልቃ ገብነት
    2025/02/24
    ጉባኤተኞቹ እንዳሉት ዓላማቸዉ የሱዳንን አንድነት፣ የሕዝቧን ሠላምና ደሕንነት በጋራ ማስከበር ነዉ።የጉባኤተኞቹን ዉሳኔ በንባብ ያሰሙት የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ ሳንዳል ሐጋር እንዳሉት ደግሞ ጦርነቶችን በሙሉ ለማቆም ቆርጠዋልምተባባሪዎቹ በአማላይ ቃላት የከሸኑትን ሥምምነትና ትብብር ገቢር ማድረግ አለማድረጋቸዉ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከቀድሞ ቀንደኛ ጠላቶቹ በተለይም ከSPLM-N ጋር መወዳጀቱ ግን የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከምዕራባዊ ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ጥግ፣ ከሊቢያ ጠረፍ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር በሚደርሱ አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ይጠቅመዋል።
    続きを読む 一部表示
    14 分